New-Site Vegetable Grain-1 Consumer_Products_2 Fence_Banner_-_PROCUREMENT-web-2 Ad_Banner2

ስለ እኛ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክስዮን ማህበር እና የግዥ አገልግሎት ድርጅትን በማቀፍ በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡

 

የንግድ ሥራ ዘርፎች

የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ

የፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራ

የግዢና ማማከር አገልግሎት

 

ዜና

ኮርፖሬሽኑ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሳምንት ላይ ተሣተፈ

ኮርፖሬሽኑ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሳምንት ላይ ተሣተፈ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባዘጋጀውና ከነሐሴ 19-23/ 2016 ዓ.ም በሚቆየው "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሳምንት ላይ ምርትና አገልግሎቱን ለጎብኚዎች አስተዋውቋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ለሃገር ውስጥና ለውጪ ገበያ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ...

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር አካሄዱ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ...

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ‹‹የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዱ ዐሻራ መርኃ ግብር አዳማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግብይት ማዕከልና በየክልሉ በሚገኙ...

የኮርፖሬሽኑ ሚኒ ሱፐርማርኬቶች ግንባታ ተጠናቀቀ

የኮርፖሬሽኑ ሚኒ ሱፐርማርኬቶች ግንባታ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ሱቆችን ወደ ሚኒ ሱፐር ማርኬት ለመቀየር በያዘው ፕሮጀክት ሶስት የሰርቶ ማሳያ ሚኒ ሱፐርማርኬቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ርክክብ አካሄደ፡፡ የሚኒ ሱፐርማርኬቶቹ ግንባታ ከዚህ በፊት ያጋጥሙ የነበሩ...

የህንጻ ሙሉ እድሳት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተካሄደ

የህንጻ ሙሉ እድሳት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተካሄደ

  የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከኩሽላደር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር የህንጻ ሙሉ እድሳት (ሪኖቬሽን) የውል ስምምነት ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ/ም አደረገ፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ...

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ገበያ የማረጋጋት ሥራዎች

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ገበያ የማረጋጋት ሥራዎች

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተለያዩ ገበያ የማረጋጋት ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ፡- ለአምራቹ ምርት ገበያ መፍጠር  ለአርሶ አደሩ ምርት የገበያ ዕድል በመፍጠር ረገድ፡- የአርሶ አደሩን ምርታማነት በቀጣይነት ለመደገፍ ኮርፖሬሽኑ 1,088,387...

የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ

የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከካይዘን ልህቀት ማዕከል ጋር የካይዘን ፕሮጀክት ትግበራ የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት መጋቢት 02/ 2016 ዓ.ም አካሄደ፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን አቶ አቻ ደምሴ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን...