ስለ እኛ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመሠረታዊ የፍጆታ ምርት አቅርቦት ገበያን የማረጋጋት፣ ለአምራቹ የገበያ ዕድል መፍጠርንና የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በወጪ ንግድ የማሳደግ ተልዕኮዎችን በመወጣት በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡

ራዕያችን

በ2025 በአፍሪካ ተወዳዳሪ፣ ተመራጭና ተደራሽ የንግድ ተቋም ሆኖ መገኘት

ተልዕኳችን

ጥራታቸውን የጠበቁና የተመረጡ የግብርናና የኢንደስትሪ ምርቶች ከሀገር ውስጥና ከውጭ በጥራት በመግዛት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ፣ ለአርሶ አደሩና አምራቹ የገበያ ዕድል በመፍጠር፣ የግብርናና የኢንደስትሪ ምርቶች ወደ ውጭ ገበያ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማሳደግ፣ የሎጂስቲክስ፣ ቴክኒክና ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችን በማቅረብ እንዲሁም የቴክኖሎጂና የሰው ሃብት ልማትን በማሳደግ በሀገራችን ቀልጣፋና ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እንዲስፋፋና ለኤኮኖሚ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረግ፡፡

 

ምርትና አገልግሎት

እህልና ቡና

የአገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋትና ለወጪ ንግድ የሚውሉ እሀሎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች

ተጨማሪ

አትክልትና ፍራፍሬ

አትክልት፣ ፍራፍሬና በፋብሪካ የተቀነባበሩ የግብርና ምርቶች

ተጨማሪ

የኢንዱስትሪ ውጤቶች

ከአገር ውስጥ አምራቾችና ከውጭ የሚገቡ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያና ሌሎች የፍጆታ ሸቀጦች

ተጨማሪ

ተጓዳኝ አገልግሎቶች

የትራንስፖርት፣ የተሽከርካሪ ጥገናና ማሽንሾፕ፣ እህል ብጠራ፣ የምድር ሚዛን፣ የቡናና ቅባት እህሎች ብጠራና ማደራጀት፣ የቡና ቀመሳና ሌሎችም ተጓዳኝ አገልግሎቶች

ተጨማሪ

ዜና

ኮርፖሬሽኑ በዓለም የጥራት ሣምንት ላይ ምርትና አገልግሎቶቹን አስተዋወቀ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አዘጋጅበት በጥራት መንደር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የጥራት ሣምንት ላይ ምርቶቹን አስተዋውቋል፡፡፡ “ጥራት፡...

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ አፈጻጸም ገመገመ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም ገመገመ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከኮርፖሬሽኑ የበላይ...

በትራንስፎርሜሽን ትግበራ ንቅናቄ ላይ የተዘጋጀ መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ንቅናቄ ላይ የተዘጋጀ መድረክ ሐምሌ 15/ 2017 ዓ.ም አካሄደ። ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጃቸው የሥልጠና ሰነዶች ማለትም የገበያ ስልት...

በ2018 በጀት ዓመት ሃገራዊ የልማት እቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞች በ2018 በጀት ዓመት ሃገራዊ የልማት እቅድ ዙሪያ ሐምሌ 17/ 2017 ዓ.ም ውይይት አደረጉ። በኮርፖሬሽኑ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ...

በምርት አቅራቢነት ከኮርፖሬሽኑ ጋር መሥራት ይፈልጋሉ?

በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ወይም በኢንዱስትሪ ውጤቶች ማምረት ሥራ ላይ ተሠማርተዋል? እንግዲያውስ የምርትዎን ተደራሽነት በማስፋት ተጠቃሚነትዎን ያሳድጉ! በአቅራቢነት ለመመዝገብ “ይመዝገቡ” የሚለውን አዝራር ይጫኑ፡፡

ይመዝገቡ

በመደብሮቻችን

በሣምንቱ ለተጠቃሚዎች የቀረቡ የአትክልት፣ የፍራፍሬና በፋብሪካ የተቀነባበሩ የግብርና ምርቶች

ከደንበኞቻችን አንደበት

“የማርታ ዱቄት ፋብሪካ ብዛት ያላቸውን የተለያዩ የስንዴ፣ ምርቶች ከተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ከባሌ፣ አሳሳና ሻሸመኔ ዙሪያ በማስመጣት አቀነባብሮ ለገበያ ያቀርባል፡፡ ድርጅታችን ከኢንሥኮ ጋር መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እን “ዘሃራ” ያሉ ልዩ ምርቶችንን ጨምሮ የተለያዩ ጥራታቸውን የጠበቁ የዱቄት ምርቶችን ለኮርፖሬሽኑ በማቅረብ፤ ኮርፖሬሽኑም ምርቶቹን ተረክቦ በማሠራጨት የገበያ ትስስር በመፍጠር ጥሩ ውጤት ማግኘት ችለናል፡፡ ባለን የገበያ ትስስር የገበያ መዋዥቅን የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልም አብረን እየሠራንም እንገኛለን፡፡ ከኢንሥኮ ባለን ግንኙነት ደስተኞች በመሆናችንም በቀጣይ ግንኙነታችን አጠናክረን ለመቀጠል እንፈልጋለን” ​
አቶ ዮሐንስ ማሞ
የማርታ ዱቄት ፋብሪካ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር (አዋሳ)