የወጪ ንግድ ምርቶች
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አገሪቱ በዓለም ላይ የምትታወቅበትን የአረቢካ ቡና ምርት ጨምሮ ልዩ ልዩ የቅባት፣ የጥራጥሬ፣ የቅመማ ቅመምና ፍራፍሬ ምርቶች በዘመናዊ መሣሪያዎች በጥራት አደራጅቶ ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ያስገኛል፡፡
ቡና ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በጣም ልዩ እና ተፈላጊ የሆኑ ቡናዎችን ታመርታለች። ከእነዚህም መካከል የሊሙ፣ ጅማ እና ይርጋጨፌ ቡናዎች በጣዕማቸው፣ በሚያድጉበት የተፈጥሮ አካባቢና አቀነባበር ልቀው ይታወቃሉ::
የሊሙ ቡና
የሚመረትበት ቦታ፡- በዋነኝነት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ዞን ውስጥ ባሉ ሊሙ ኮሳ እና ጌራ አካባቢዎች
መለያ ባህሪያት
– ፍሬው፡- ከመካከለኛ እስከ ትልቅ
– አሲዲቲ፡- በቀላሉ የመለታወቅና ከወይን ጣዕም ጋር ተመሳሳይነት ያለው
– ቃና፡- ከካራሜል ወይም ማር ጋር የሚቀራረብ
የማቀነባበሪያ ዘዴ
– አብዛኛው የታጠበ ሲሆን ይህም ጥርት ያለ እና ተለይቶ የሚታወቅ አሲዲቲ ይሰጠዋል።
-ከ1,500–2,000 ሜትር በላይ በሆነ ከፍታ ስለሚመረት ልዩ ልዩ ጣዕም አለው።
– አማካይ ጣዕም ስላለው ለኤስፕሬሶ እና ፊልተር ቡና ተስማሚ ነው።
የጅማ ቡና
የሚመረትበት ቦታ፡- በደናማ የዕጽዋት ሽፋኑ በሚታወቀው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጅማ ዞን፡፡
መለያ ባህሪያት
– ፍሬ፡- ከበድ ያለና የሲረፕ ባህሪ ያለው
– አሲዲቲ: ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ
– የቼኮሌትና የቅመም (በተለይም የካካዎና ቀረፋ ዓይነት) ቃና አለው
የማቀነባበሪያ ዘዴ
– ብዙውን ጊዜ በተፈጥሯዊ ዘዴ (በደረቁ) ይዘጋጃል፤ ይህም ጠንካራ እና የጫካ ጣዕሙን/ቃናውን ያጎላዋል።
– ከ1,400–1,800 ሜትር ከፍታ ላይ ስለሚመረት ጥልቅ ጣዕም አለው።
– ጠንካራ (ከበድ ያለ) ጣዕም ስላለው ቀላቅሎ ለመጠቀም ይውላል፡፡??
የይርጋጨፌ ቡና
የሚመረትበት ቦታ፡- በደቡብ ኢትዮጵያዋ ሲዳማ ይርጋጨፌ አካባቢ በከፍታ ላይ በሚገኙ እርሻዎች ላይ ይመረታል።
መለያ ባህሪያት
– መጠን: ከቀላል እስከ መካከለኛ
– አሲዲቲ: በቀላሉ የሚለይና የሲትረስ አሲድ አይነት
– ቃና: የተለያዩ አበቦችና ፍራፍሬ እንዲሁም የሻይ ዓይነት ያለው
የማቀነባበሪያ ስልት
– አብዛኛው የታጠበ ሲሆን ይህም ንፁህ እና የጠራ ጣዕም ይሰጠዋል።
– ከባህር ወለል በላይ ከ1,700–2,200 ሜትር በላይ ከፍታ ባላቸውና በከፍታቸው በታወቁ የኢትዮጵያ ቦታዎች ይመረታል፡፡
– በዓለም ከሚገኙ በአንድ ስፍራ ብቻ የሚመረቱ የቡና ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ሌሎች መጠጦች ላይ ቀላቅሎ ለመጠጣት ለመጠቀም፣ በኤሮፕረስ ለማዘጋጀትና በቀዝቃዛ ቡናነት ለመጠቀም ተስማሚ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 0910335808 ይደውሉ፡፡
