በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ አፈጻጸም ገመገመ

    በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም ገመገመ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራር ጋር መድረክ በመፍጠር የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በመፈተሽ ግብረ መልስና የሥራ አቅጣጫ ሰጥቷል::

    በመድረኩ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር አቶ መለስ መና ለኮርፖሬሽኑ የተመደበው አዲስ አመራር በኦፕሬሽን፣ በውጭ ምንዛሪ፣ በአሰራርና በአደረጃጀት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አቅዶ እየሰራው ባለው የሪፎርም ሥራ የታየው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አክለውም ኮርፖሬሽኑ በዋጋ ማረጋጋት እየሰራ ያለውን ሥራ በልዩ ትኩረት ማከናወን እንዳለበት በመጠቆም የኮርፖሬሽኑን አሰራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፍ እንዳለበት በማስገንዘብ ቋሚ ኮሚቴውም ለኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡