ኮርፖሬሽኑ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድሬዳዋ ከተማ አካሄደ

    የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በመተባበር 7ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሐምሌ 22/ 2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አካሄደ፡፡

    የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሃይሉ ንጉሴ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት አረንጓዴ አሻራ ትውልድ የማስቀጠልና ያለማስቀጠል ጉዳይ መሆኑን በማስመር ባለፉት ዓመታት በዚህ ረገድ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ እንደቆዩና ኮርፖሬሽኑም ሲሳተፍ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ኮረፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሚያደርግ እንደመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ ምርቶችን በብዛትና በጥራት ለገበያ በማቅረብ ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

    በኮርፖሬሽኑ የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሃመድ ሸምሱ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ በርካታ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቁመው በተለይም እንደ ሃገር ስኬት የታየበት የቡና ምርት ጥላ የሚፈልግ በመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡