የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ

    የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የዘንድሮውን ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በንፋስ ስልክ-ላፍቶ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሐምሌ 24/ 2017 ዓ.ም አካሄዱ፡፡ በአረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ -ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዓመታት ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በመንግስት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡

    በዘንድሮው መርሃ ግብር አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞችን ተሳታፊ በማድረግ በተለያዩ የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎችና የተመረጡ ቦታዎች ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አያይዘውም ከቀናት በፊት በድሬዳዋ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያና የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡