
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አዘጋጅበት በጥራት መንደር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የጥራት ሣምንት ላይ ምርቶቹን አስተዋውቋል፡፡፡
“ጥራት፡- በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 11–15/2018 ዓ/ም በተካሄደውና ከ150 በላይ የአገር ውስጥ አምራቾችን ባሳተፈው ርዕይ ላይ ኢንሥኮ ጥራታቸውን የጠበቁ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎችና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምርቶችን ለሸማቹና ህብረተሰብና የማስተዋወቅና የገበያ ትስስር የመፍጠር ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ በመርኃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ጥራት በአንድ ጀምበር የሚረጋገጥ ሂደት ሳጥሆን ጥራት ባለው እሳቤ በሚመራና ጥራት ያላቸውን የአሠራር ሥርዓቶች በሰውጡ ባካተተ አገነባብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ የሚሄድ ባህል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም ረገድ መንግሥት ጥራትን በሁሉም የአገልግሎትና የንግድ ዓይነቶች የማምረት ሂደት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ መሆኑን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአገሪቱ ምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት እያረጋገጠ የመጣውን ፍጥነት መመገብ የሚችል የጥራት አገልግሎት መስጠት የሚቻልበትን አቅም መገንባት መቻሉን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመጠንና በዓይነት እየጨመረ ከመጣው የአገሪቱ የወጪ ንግድ መጠንና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ጀርባ ዓለም አቀፍ ተጠባቂ የጥራት ደረጃዎች እንዲረጋገጡ ያስቻሉ የጥራት አገልግሎት ማረጋገጫ ፋሲሊቲዎች ግንባታና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ዓይነተኛ ሚና መጫወታቸውን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይም መንግሥት የመጀራቸውን ጥራትን የማስጠበቅና ሥራዎችና የፋሲሊቲ ግንባታዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ለአራት ቀናት በተካሄደው ርዕይ መገባደጃ ላይ ኮርፖሬሽኑ ላሳየው ንቁ ተሣትፎ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል::






