በግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ሥልጠና ተሰጠ

በግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ለኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ከታህሳስ 23-24/ 2018 ዓ.ም ተሰጠ፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚመሩበት የግዢ አፈጻጸም መመሪያ በገንዘብ ሚኒስቴር መዘጋጀቱን በመጥቀስ ወደ ስራ ከመገባቱ በፊት መመሪያው ምን ይላል የሚለውን መገንዘብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመመሪያው ዝግጅት ወቅት የኮርፖሬሽኑን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን መደረጉንም አያይዘው አንስተዋል፡፡

በግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ የተዘጋጀውን ሥልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት ገበያው ይታይህ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የፕሮኪውርመንት ኢኒሺዬቲቭ ኦውነር ሲሆኑ መመሪያው የመንግስት የልማት ድርጅቶችየግዢ አፈጻጸም መመሪያ 1070/ 2017 እንደሚባል ገልጸው መመሪያው ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ በአፈጻጸም ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ሥልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡