የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ የተመረጡ የብርዕ፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን እንዲሁም ቡናን ከአገር ውስጥ አምራቾች በመግዛት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል፤ ለሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት ለልዩ ልዩ ተቋማት የግብርና ምርቶች አቅርቦት ያካሂዳል፡፡ አርሶ አደሩ የእህል ማምረት ፍላጎቱን በማሳደግና ገበያ መፍጠር፣ ለህብረተሰቡም የእህል ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ግብይቱን ለማድረግ ይሠራል፡፡
ለሀገር ውስጥ ገበያ ማረጋጊያ የሚውሉ የምግብ እህሎች
- ጤፍ
- የሀገር ውስጥና የውጭ ስንዴ
- በቆሎና ገብስ
- ሌሎችም
ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች
- የታጠበ ቡና (የሲዳማ፣ የይርጋጨፌ፣ የነቀምት፣ የሊሙ)
- ያልታጠበ ቡና (የሐረር፣ የሲዳማ፣ የጅማ፣ የቴፒ፣ የነቀምት)
- የቅባት እህሎች (ነጭ የወለጋና የሁመራ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ተልባ)
- ጥራጥሬ (ነጭና ቀይ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ፣ ሽምብራ)
ለተጨማሪ መረጃ 0911633747 ይደውሉ፡፡
