ተጓዳኝ አገልግሎቶች
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከመደበኛው የምርት በተጨማሪ ለአገር ውስጥ ደንበኞች የሥልጠናና ማማከር፣ የትራንስፖርት፣ የእህል ብጠራና ማደራጀት፣ የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ጥገናና ማሽንሾፕ እንዲሁም የቡና ቀመሳ ላቦራቶሪ አገልግሎቶችን ለውጭ ለጠቃሚዎች ይሰጣል፡፡
በሥልጠና አገልግሎት አገልግሎት ዘርፍ የሚሰጡ ሥልጠናዎች
– ለጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላት የሚረዳ የግዥ ሥልጠና፣
– የውል አስተዳደር
– የግዥና አቅርቦት
– የንብረት አስተዳደር
– የገቢና የወጭ ንግድ ፕሮሲጀር
እንዲሁም በደንበኞች ፍላጎት ያተኮረ ላይ የተመሠረተ ስልጠና በመቅረጽ በተግባር ላይ የተደገፈ ሥልጠና ይሰጣል፡፡
የማማከር አገልግሎት
– የግዥና ከግዥ ጋር ተያያዝ የሆኑ መመሪያዎች ማዘጋጀት
– የንብረት አስተዳደር መመሪያዎች ማዘጋጀት
– የቴክኒክ ፍላጎት (Technical Specification) ማዘጋጀት
የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት
በመስኩ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎችና የተሟሉ መሣሪያዎች በመታገዝ የተሟላ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት
የወርክሾፕ አገልግሎት
- ለቀላልና አነስተኛ የጭነት መኪኖች ደረጃውን የጠበቀ ስፖንዳ መሥራት
- ተንቀሳቃሽ ሱቆችን ማምረት
- የተለያዩ ማሽኖችን በመጠቀም የማምረትና ሌሎች የማሽን ሥራዎች
የእህል ብጠራ አገልግሎት
በአዲስ አባባና በክልል ከተሞች በሚገኙ የቀለም መለያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ ማሽኖች በደንበኛው ፍላጎት መሠረት በከፍተኛ ጥራት የእህልና ቡና ማበጠር አገልግሎት
የምድር ሚዛን አገልግሎት
በአዲስ አባባና በክልል ከተሞች (ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ አሰላ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጊኒር፣ ኢተያ፣ ሻሸመኔ፣ ነቀምት፣ በደሌ) በሚገኙ ዘመናዊ የምድር ሚዛኖች ቀልጣፋ የምዘና አገልግሎት
የእህል ህክምና (Fumigation)
ጭነት የማጓጓዝ አገልግሎት
– ከ35 እስከ 400 ኩንታል የመጫን አቅም ባላቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ደረቅ ጭነት የማጓጓዝ አገልግሎት
– የሚበላሹ ምርቶችን ማቀዝቀዣ ማሽን በተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች የማጓጓዝ አገልግሎት
የቡና ጣዕም ላቦራቶሪ አገልግሎት
በዘመናዊ ላቦራቶሪና የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የታገዘ የቦና ቀመሳ አገልግሎት
ለተጨማሪ መረጃ 0114 42 05 94 | 0114 70 88 00 | 0114 40 25 35 | 0114 40 17 63
