የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ሱቆችን ወደ ሚኒ ሱፐር ማርኬት ለመቀየር በያዘው ፕሮጀክት ሶስት የሰርቶ ማሳያ ሚኒ ሱፐርማርኬቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ርክክብ አካሄደ፡፡

የሚኒ ሱፐርማርኬቶቹ ግንባታ ከዚህ በፊት ያጋጥሙ የነበሩ የአትክልትና ፍራፍሬ ብክነቶችን ለመከላከልና ነባር ኮንቴይነሮችን ለማዘን እንደሆነ በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ሚኒ-ሱፐርማርኬቶቹ በዘመናዊና ጥራት ባላቸው ማቴሪያሎች የተሰሩ ሲሆን ሰርቪሊያንስ ካሜራ (እያንዳንዳቸው ስምንት ካሜራ ያላቸው)፣ የአትክልትና ፍራፍሬ መደርደሪያ፣ የተበላሹ ምርቶች የሚለዩበትና የሚወገዱበት ክፍል እንዲሁም ስፖት ላይት ያላቸው ናቸው፡፡

ሚኒ ሱፐር ማርኬቶቹ ግሎባል በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት፣ ቄራ በሚገኘው የአትክልትና ፍራፍሬ ማከፋፈያ እና በአለም ባንክ የሚገኙ ሲሆን በቅርቡ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

003

002

001