የፕሬስ መግለጫ

ጥር 28 ቀን 2016 /

አዲስ አበባ

ኮርፖሬሽኑ 2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዓመት 1.04 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለገበያ አቀረበ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ብር 5,337,522,670 ዋጋ ያለው 1,000,513 ኩንታል መሠረታዊ ምርትና አገልግሎት ለማሰራጨት አቅዶ ብር 5,819,644,863 ዋጋ ያለው 1,043,710 ኩንታል ምርትና አገልግሎት በማሰራጨት ዕቅዱን በመጠን 104 በመቶ በዋጋ ደግሞ 109 በመቶ አከናውኗል፡፡

በሀገር ውስጥ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ብር 3,899,901,069 ዋጋ ያለው 645,327 ኩንታል ምርትና እና የአገልግሎት ሽያጭ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ አቅዶ ብር 3,981,531,133 ዋጋ ያለው 656,038 ኩንታል ምርት እና የአገልግሎት ስርጭት በማከናወን የዕቅዱን በመጠን ሆነ በዋጋ 102 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ላይ በውጭ ገበያ 355,186 ኩንታል እህልና ቡና በብር 1,437,621,601 ለመሸጥ አቅዶ 387,673 ኩንታል ስንዴ፣ ሰሊጥ እና ቡና በብር 1,838,113,730 (32,835,355 የአሜሪካን ዶላር) በመሸጥ የዕቅዱን በመጠን 109 በመቶ በዋጋ ደግሞ 128 በመቶ አከናውኗል፡፡

የግዥ አፈጻጸምን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በስድስቱ ወራት በአጠቃላይ ሊገዛው ያቀደው መሠረታዊ የምርት አቅርቦት መጠን ብር 2,663,702,896 ዋጋ ያለው 630,157 ኩንታል ሲሆን በዚህ ወቅት ብር 4,059,745,342 ዋጋ ያለው 673,170 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 107 በመቶ በዋጋ ደግሞ 152 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመጀመሪያው የበጀት ዓመት አጋማሽ ከሀገር ውስጥ ምንጮች ያከናወነው ግዥ 558,949 ኩንታል ሲሆን ከዚህ ውስጥ 412,382 ኩንታል ወይም 73.8 በመቶ የእህልና ቡና፣ 50,450 ኩንታል ወይም 9.0 በመቶ የፍጆታ ዕቃ፣ 38,943 ኩንታል ወይም 7.0 በመቶ የፍራፍሬ እና አትክልት እንዲሁም 57,175 ኩንታል ወይም 10.2 በመቶ የኮንስትራክሽን ግብዓት ግዥ ነው፡፡

ለአምራቹ ምርት ገበያ በመፍጠር የተከናወኑ ተግባራት፡-

ከኮርፖሬሽኑ ቁልፍ ተግባራት አንዱ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በቀጣይነት መደገፍና ለምርቱ አስተማማኝ ገበያ መፍጠር ሲሆን በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ቀደም ብሎ ወደ አዲስ ምርት ግዥ በመግባት 392,210 ኩንታል እህልና 1,077 ቡና እንዲሁም 38,981 ኩንታል ፍራፍሬ እና አትክልት ከምርት አቅራቢዎች ግዥ አከናውኗል፡፡

በሌላም በኩል የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ያመረቱትን ምርት ተቀብሎ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማሰራጨት በግማሽ ዓመቱ   126,720 ኩንታል ምርት በመግዛት ለአምራቹ የገበያ ዕድል ፈጥሯል፡፡

የአቅርቦት እጥረትንና የዋጋ ንረት ለመከላከል የተደረገ ጥረት፡-

ኮርፖሬሽኑ የምርት አቅርቦት እጥረትንና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ገበያውን ለማረጋጋት ለመንግሥት ሠራተኞች፣ ለማረሚያ ቤቶችና ለሌሎች ሸማች የህብረተሰብ ከፍሎች ብር 74,541,036 ዋጋ ያለው 11,348 ኩንታል ጤፍ፤ ብር 222,098,577 ዋጋ ያለው 34,389 ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ፤ ብር 1,000,293,075 ዋጋ ያለው 9,231,300 ሊትር የምግብ ዘይት፤ ብር 174,470,803 ዋጋ ያለው 27,201 ኩንታል ስኳር እና ብር 784,334,763 ዋጋ ያለው 83,118 ኩንታል ልዩ ልዩ የፍጆታ ሸቀጦች በማሰራጨት የተጠቃሚውን ህብረተሰብ የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ጥረት አድርጓል፡፡

በተጨማሪም የምርት አቅርቦት እጥረትን ለመሸፈን በተለይም ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና ለዓለም ምግብ ድርጅት ብር 240,016,955 ዋጋ ያለው 74,754 ኩንታል በቆሎ ተሠራጭቷል፡፡

በግንባታው ዘርፍ የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትንና ዋጋ ንረትን ለመከላከል ከፋብሪካዎች 56,915,287 ዋጋ ያለው 58,257 ኩንታል በቀጥታ በመረከብ ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ማሠራጨት ችሏል፡፡

የሸማቹን ገበያ የማረጋጋት አሰተዋፅዖ በገንዘብ ሲመዘን፡-

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አምራቹ ላመረተው ምርት ገበያ ከመፍጠር ባሻገር ከፍጆታ ሸቀጦች ጋር ያለዉን የዋጋ መወደድ በተለይም በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ በዓላት ወቅት በርካታ የፍጆታና ሌሎች ሸቀጦች ግዥ ሸማቹ ማህበረሰብ በስፋት የሚያከናውንበት ሁኔታ በመኖሩና ለዚህም ዝግጅት በማድረግ ገበያዉን ለማረጋገት የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በዚህ መሠረት 9,231,300 ሊትር የምግብ ዘይት፣ ስኳር 27,201 ኩንታል፣ ሩዝ 13,160 ኩንታል፣ ቀይ ሽንኩርት 224 ኩንታል፣ ጤፍ 11,348 ኩንታል እና ሌሎችም ምርቶች ከገበያው ዋጋ በጠቅላላ ብር 1,388,799,021 ቅናሽ በማድረግ ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡

 

--//--