ራዕይ

መሠረታዊ የምግብ ፍጆታ፣ ልዩ ልዩ ምርትና ሸቀጥ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብና በማሠራጨት የሀገር ውስጥ ገበያን በማረጋጋት በ2022 ተመራጭ የልማት ድርጅት ሆኖ መገኘት፡፡

ተልዕኮ

  • የተመረጡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በማቅረብ የሀገር ውስጥ ገበያን ማረጋጋት፣ ለአርሶ አደሩና አምራቹ የገበያ ዕድል መፍጠር፤
  • የግብርና ምርቶችን ወደ ውጪ ገበያ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት
  • የውክልና ግዥ ማካሄድናየግዥ ማማከርና የሥልጠና አገልግሎት መስጠት፤
  • በሀገራችን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የንግድ ስርዓት እንዲስፋፋ እና ለኢኮኖሚ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ፡፡

 

ዕሴቶች

 

  • ጥራትና ተመራጭነት
  • በቡድን መስራትና ዉጤታማነት
  • ደንበኛ ተኮር አገልግሎት
  • ሃላፊነትና ተጠያቂነት
  • ተደራሽነትና ወጭ ቆጣቢነት
  • ለፈጠራና አዳዲስ አሰራር ትጉነት

ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች

  • የተመረጡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችንና፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር በተወዳዳሪ ዋጋ ገዝቶ በማሰራጨት የአገር ውስጥ ገበያን ማረጋጋት፤
  • ሰብል፣ አትክልት እና ፍራፍሬ በተመረጠ አኳኋን ማስመረት፣ መግዛትና ማሰራጨት፤ ክምችት መያዝ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ ማቅረብ፤
  • በወቅታዊ የገበያ መረጃ ላይ ተመስርቶ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ግዢዎችን መፈፀም፣ መሸጥ፤
  • የአርሶ አደሩ የማምረት ፍላጎት እንዲያድግ ለግብርና ምርቶች አስተማማኝ ገበያ እንዲፈጠር እገዛ ማድረግ፤
  • ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የግብይት አሠራር መዘርጋትና መፈፀም፤
  • ለሥራው የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የምርምር፣ የትምህርትና የስልጠና ተቋማት ጋር መተባበር፤
  • የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግዢዎችን በሚመለከት የምክር አገልግሎት መስጠት፣ የውክልና ግዢ መፈፀምና ሥልጠና መስጠት፤
  • የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ቦንድ የመሸጥ፣ የመግዛት፣ በዋስትና የማስያዝ፤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፤
  • ከተቆጣጣሪው ባለስልጣን በሚሰጠው አቅጣጫ ላይ በመመሥረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የሰው ኃብት፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ ሥራ አመራር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለው ኢንቨስትመንት መሳብም ሆነ በኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍን ጨምሮ ጥናት በማካሄድ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
  • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን መፈጸም፡፡