GL.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ‹‹የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዱ ዐሻራ መርኃ ግብር አዳማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግብይት ማዕከልና በየክልሉ በሚገኙ ቅርንጫፎች ከ11,500 በላይ የፍራፍሬ፣ ቡናና የጥላ ዛፍ ችግኞችን በመትከል አሳልፈዋል፡፡

‹‹አረንጓዴ ዐሻራችን የነገ ዋስትናችን›› በሚል ተቋማዊ መሪ ቃል በአዳማ የግብይት በተካሄደው ዓቢይ መርኃ ግብር መክፈቻ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ባደረጉት ንግግር፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ በውጤታማነት መካሄዱንና ይህም ጤናማ የአየር ንብረት እንዲኖርና የአካባቢ ደኅንነት ውጤታማነት እንደ ሀገር እንዲያድግ ዕድል የሰጡ መሆኑን ጠቁመው እንደ ተቋም እስካሁን በተካሄዱ መርኃ ግብሮችም በመላው ሠራተኛ ተሣትፎና እንክብካቤ ከ40 ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለው 31 ሺህ ይህሉ መጽደቃቸውን አስታውሰዋል፡፡

በዘንድሮውም መርኃ ግብርም መላው ሠራተኛው የከዚህ ቀደም ልምዱን መነሻ በማድረግ ለቀጣዩ ተውልድ የተሻለ ሕይወት ዕድል የመፍጠር የራሱን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አምርና ሠራተኞች ከችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ በተጓዳኝ የአዳማ የግብይት ማዕከልን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

#GreenLegacy #አረንጓዴዐሻራ #ETBC