Palm_Oil_-_Imported.jpg

 

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመንግሥት ድጎማ ከውጭ ለማስገባት በዕቅድ ከያዘው 12.5 ሚሊየን ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ውስጥ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ/ም የገባውን 2.4 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጨምሮ በሦስት ዙር 7.2 ሚሊየን ሊትር ወደ ሃገር ውስጥ ገብቶ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ በጅቡቲ ወደብ ላይ የደረሰው 5.3 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሁለት ዙር በቅርቡ ወደ ሃገር ውስጥ ይገባል፡፡

 

ፓልም የምግብ ዘይቱ ባለ ሶስት፣ አምስትና ሃያ ሊትር ሲሆን የምግብ ዘይቱን ተረክበው ለህብረተሰቡ ለማሰራጨት መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ/ም በቃሊቲ የፍጆታ ዕቃዎች ማከፋፈያ መደብር የተገኙ የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ፓልም የምግብ ዘይት በተመደበላቸው ኮታ መሰረት ተረክበዋል፡፡

 

አቶ ተውፊቅ ይመር የፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት የምግብ ዘይቱ በትክክል ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ልዩ ክትትል ያስፈልጋል፡፡ ተገዝቶ መቅረቡ ብቻ በቂ አይደለም ያሉት ኃላፊው ሥርጭቱን በአግባቡ ለማከናወን ኮርፖሬሽኑ ሙያው በሚጠይቀው ሥነ-ምግባር መሰረት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡