ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከአራቱም ዘርፎችና ከዋና መ/ቤት የተውጣጡ ሴት ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአንድነት ፓርክ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ/ም ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

ጉብኝቱን ያዘጋጀውና ያስተባበረው የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት አለማየሁ ከየዘርፉና ከዋና መ/ቤት የተወከሉ ሴት ሰራተኞች በጉብኝቱ መሳተፋቸውን ገልጸው በስራቸው የበለጠ ውጤታማ እና ጠንካራ እንዲሆኑ ለማገዝ በጽ/ቤቱ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም ኮርፖሬሽኑ የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በጉብኝት እያከበረ መሆኑን ጠቅሰው ይህም በየዘርፉና በዋና መ/ቤት ያሉ ሴት ሰራተኞችን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉና ያነጋገርናቸው ሰራተኞች በአንድነት ፓርክ በመገኘት የሀገራቸውን ታሪክና የተፈጥሮ ሃብት በመመልከታቸውና በአጠቃላይ በጉብኝቱ መዘጋጀት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

March_8_DSC_7441.JPG