11a.jpg11b.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞች በ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና በ2016 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡ በውይይት መድረኩ የዋና መ/ቤት፣ የአራቱም ዘርፎችና የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ የክልል ግብይት ማእከላትና ጣቢያዎች አመራርና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የውይይት መድረኮቹ በድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ መቀሌ፣ አዳማ እና አዲስ አበባ ከተሞች በጥቅምት እና ህዳር 2016 ዓ.ም ተካሂደዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከህዳር 10-11/ 2016 ዓ.ም በተካሄደው የውይይት መድረክ መክፈቻ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በ2015 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑን የሚያሻግሩ እቅዶች ተነድፈው ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው ከቀደሙ ዓመታት የላቀ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ የተገኘው ስኬት የጠቅላላ አመራርና ሰራተኞች ውጤት መሆኑን ጠቁመው ይህም ለሌላ ውጤት የሚያነሳሳ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ክንውን ሪፖርት፣ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች፣ የተወሰዱ መፍትሔ እርምጃዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከሰራተኞች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ዋና ሥራ አሥፈጻሚው በመድረኩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልእክት በ2016 በጀት ዓመት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ግዥን ሳያቋርጡ ማከናወን፣ ሽያጭን በስፋት ማካሄድ፣ ፈጣን አገልግሎት መስጠት፣ የተለያየ የገበያ ትስስር መፍጠር የሚሉት በዋናነት ይገኙበታል፡፡