ከኮርፖሬሽኑ ምስረታ ጀምሮ በእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ፍርዱ አየለ እና በግዥና ማማከር አገልግሎት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚነት ያገለገሉት አቶ ክፍሌ ተስፋዬ ከኮርፖሬሽኑ በጡረታ ምክንያት በመልቀቃቸው የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ኅዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም በግሎባል ሆቴል ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡


በሽንት ፕሮግራሙ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በጡረታ ምክንያት ኮርፖሬሽኑን የለቀቁትን የቀድሞ ስራ አስፈጻሚዎች ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ቀሪ ጊዜያቸውን ከቤተሰባቸው ጋር በደስታ እንዲሳልፉ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡


አቶ ፍርዱ አየለ ባስተላለፉት መልእክት በኮርፖሬሽኑ ውስጥ በነበራቸው ኃላፊነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተሰጣቸው እውቅና የነሱ ብቻ ሳይሆን አሁን ላለው የስራ አመራር አባል ሁሉ መሆኑን ጠቁመው የተደረገው ሽኝት ለካ ልፋቴ ዋጋ አለው እንድል አድርጎኛል ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡


አቶ ክፍሌ ተስፋዬ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ እውቀት ያገኙበት ቦታ እንደሆነ ጠቅሰው በአካል ቢርቁም በመንፈስ ግን ሁሌም ከኮርፖሬሽኑ ጋር እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

9b.jpg9a.jpg