የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዕውቅናውን ያገኘው ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን ምዕተ ዓመት አከባበር በማስመልከት “ማኅበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ቃል በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከኅዳር 24 እስከ 26/2016 ዓ/ም ሲካሄድ በቆየው የ2016 የአሠሪና ሠራተኛ ጉባዔ መገባደጃ ላይ በተካሄደው የዕውቅና መርኃ ግብር ነው፡፡

ከ200 በላይ በግብርና፣ በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ ምቹ የሥራ ሁኔታ ለፈጠሩ የግልና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ አሠሪዎች እንዲሁም የሠራተኞች ፌዴሬሽኖች በተወዳደሩበት በዚህ የዕውቅና መርኃ ግብር ላይ ኮርፖሬሽኑ ብልጫ ካገኙ ተቋማት መካከል አንዱ በመሆን ዕውቅና አግኝቷል፡፡

ሽልማቱን የኮርፖሬሽኑ የሕግ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችና አሠራር ማሻሻያ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ከሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እጅ ተቀብለዋል፡፡ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ክብርት ሚንስትሯ ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠርና ሠላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዕውቅናውን በተመለከተ አቶ ይርጋሸዋ በሰጡት አስተያየት ኮርፖሬሽኑ ለሠራተኛው ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ እንደ ካይዘን ያሉ የለውጥ መሣሪያዎችን ጭምር በመጠቀም እየሠራ መሆኑን፤ አንዲሁም ከሠራተኛ ማኅበሩ ጋር ዘላቂ የሆነ መልካም ግንኙነትን እንዲኖር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሠራተኛውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሠፊ ሥራዎችን ማከናወኑን አስረድተዋል፡፡ የተገኘው ዕውቅናና ሽልማትም በቀጣይ በመስኩ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለማጠናከር የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ በካይዘን ትግበራና ውጤታማነት እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ዘርፍ አገግሎት አሰጣጥ ባበረከተው አስተዋጽዖ ተሸላሚ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ይርጋሸዋ፤ አሁንም የተገኘው የዕውቅናና ሽልማት ምቹ የሥራ አካባቢን ለሠራተኛው ከመፍጠር ባለፈ በሌሎች መስኮችም ውጤታማ አፈጻጸምን በማጎልበት ኮርፖሬሽኑ ምርትና አገልግሎቱን በተሻለ ጥራትና ተደራሽነት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ የሚያበረታታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

7a.jpg

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 7b.jpg