የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በህዳር ወር 2016 ዓ.ም 280,248 ኩንታል ምርት ለገበያ አቀረበ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በወሩ የምርት ግዥና ሽያጭ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የግዥ ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ሕዳር ወር 101,124 ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍጀታ ዕቃ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት በብር 515,030,325 ለመግዛት አቅዶ 48,150 ኩንታል ምርት በብር 299,343,563 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 48 በመቶ በዋጋ ደግሞ 58 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 477,599 ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የፍጆታ ዕቃዎች ለመግዛት አቅዶ የነበረ ሲሆን 593,917 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን 124 በመቶ ማከናወን ተችሏል፡፡

የአጠቃላይ ሽያጭ አፈጻጸምን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ሕዳር ወር በሀገር ውስጥ እና በኤክስፖርት ገበያ ለመሸጥ ያቀደው የእህል፣ ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና አትክልት እና ፍራፍሬ ምርት መጠን 125,234 ኩንታል በብር 718,853,059 ሲሆን 280,248 ኩንታል በብር 1,360,169,866 በመሸጥ ዕቅዱን በመጠን 224 በመቶ እንደዚሁም በዋጋ 189 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በወጭ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ለመሸጥ ያቀደው አጠቃላይ መጠን 555,837 ኩንታል ምርት ሲሆን የተሸጠው መጠን 946,502 ኩንታል ወይም የዕቅዱን 170 በመቶ ነው፡፡

GridArt_20231012_110101692.jpg