report.jpg

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ሰባት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ ገበያ ለመሸጥ ካቀደው 2.29 ሚሊዮን ኩንታል የእህልና ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት 2.27 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወይም የዕቅዱን 99 በመቶ ለገበያ አቀረበ፡፡ በተለይም በሀገር ውስጥ ለመሸጥ ያቀዳቸዉ ልዩ ልዩ ሸቀጦች መጠን 1.69 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን በዚህ ወቅት መሸጥ የተቻለው 2.05 ሚሊዮን ኩንታል ወይም የዕቅዱን 107 በመቶ እንደሆነ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ 1.23 ሚሊዮን ኩንታል እህልና ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ፍጆታ ዕቃዎች ከሀገር ውስጥ አምራቾች ለመግዛት አቅዶ 944 ሺህ ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን 77 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የአቅርቦትና የግብይት ችግር የሚስተዋልባቸውና በአጭር ጊዜ የሚበላሹ የግብርና ምርቶች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 211 የመገበያያ ማዕከላት ምርቶችን ከአምራቹ በቀጥታ በመግዛት ለሸማቹ እያቀረበ ይገኛል፡፡ እስከ 900 ኪሎሜትር ርቀት በመጓዝ ከፍተኛ የግብርና ምርት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች ለአምራቹ ተገቢውን ዋጋ ሰጥቶ በመግዛት የምርት እጥረት ወደ አለባቸው አካባቢዎች በማጓጓዝ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ያቀርባል፡፡ ይህም በመደረጉ አምራቾች በገበያ እጥረት ምክንያት ምርታቸው እንዳይበላሽና ባመረቱት ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትልቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ሸማቹ ህብረተሰብንም ከመደበኛ ገበያው የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

 

የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችችን በመቀላቀልና ድረገጻችን በመጎብኘት የምርትና አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉና በፍጥነት ያግኙ!

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/etbcofficial
ቴሌግራም፡- https://t.me/etbcinfo
ዜና ኢንሥኮ አንድሮይድ መተግበሪያ፡- https://t.ly/DiXR
ዩትዩብ ቻነል፡- https://www.youtube.com/@etbcinfocom4858

አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ያድርሱን፡፡

ኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Cold_Store_01.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ የሚያስችል ማቀዝቀዣ መጋዘንን ጨምሮ ሁለገብ ሕንጻ ለማስጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ-ስርዓት የካቲት 25/2015 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሺ ቶታል ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ይዞታ ውስጥ አከናወነ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሁለገብ ህንጻው ግንባታ ከ 1.24 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚሰራና የሕንጻው ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አያይዘውም በተለይም የማቀዝቀዣ ግንባታው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሳይበላሹ፣ ጥራታቸውን እንደጠበቁ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚው ጋር እንዲደርሱ ለማድረግ እና አምራቹ ምርቱ ገበያ እንዲያገኝ ለማበረታታት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀሰን ሙሁመድ በበኩላቸው የሚገነባው ህንጻ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም መሆኑን በመጠቆም የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን እለት ታሪካዊ ቀን ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ህንጻው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በትጋት እንዲሰሩ ጠይቀው የስራ አመራር ቦርዱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የሚገነባው ሕንጻ ሁለት መሰረት ያለው ባለ አስር ወለል ቅይጥ የአገልግሎት ህንጻ እና ዘመናዊ ባለማቀዝቀዣ መጋዘን የያዘ ሲሆን በተጨማሪም የገበያ ማዕከል፣ ላቦራቶሪዎች እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራን ያካተተ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተግበር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች አቅርቦትን በጥራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ወቅት ተመላክቷል።

Cold_Store_02.jpg

 Mixed-Use-BLDG-2.jpg

02.jpg

 

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከየካቲት 16-20/2015 ዓ.ም "የወጪ ንግድ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ባለው ዓውደ ርዕይ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

ዓውደ ርዕዩ የአገራችንን የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በአጠቃላይ ለአገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ተሳታፊ ለሚሆኑ ጎብኝዎች ማስተዋወቅን ዓላማው አድርጓል፡፡ በዓውደ ርዕዩ ላይ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት አምራቾች በመሳተፍና ግብይት በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለገበያ የሚያቀርባቸው ጥራታቸውን የጠበቁ የቡና፣ የቅባት እህል፣ የጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ምርቶች፣ ልዩ ልዩ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩና የግብርና መሠረታዊ ምርቶችን፣ ለህብረተሰቡ ፍጆታ የሚውሉ መሠረታዊ የምግብን የንጽሕና መጠበቂያ ሸቀጦችና ሌሎችንም ምርቶቹን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡

01.jpg03.jpg

 

የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችችን በመቀላቀልና ድረገጻችን በመጎብኘት የምርትና አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉና በፍጥነት ያግኙ!

ድረገጽ፡- https://www.etbc-ethiopia.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/etbcofficial
ቴሌግራም፡- https://t.me/etbcinfo
ዜና ኢንሥኮ አንድሮይድ መተግበሪያ፡- https://t.ly/DiXR
ዩትዩብ ቻነል፡- https://www.youtube.com/@etbcinfocom4858

አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ያድርሱን፡፡
ኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

 

 

 

Trucks.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚያከናውናቸውን የግብይት ሥራዎች ለማሳለጥ የሚያገለግሉ ተጨማሪ አራት ከባድ ተሽከርካሪዎች ግዢ አከናወነ፡፡ የተሽከርካሪ ርክክቡ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በተከናወነበት ወቅት አንደተገለጸው የተገዙት ተሽከርካሪዎች እያንዳንዳቸው 50 ኩንታል፣ በድምሩ 200 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ከ11.4 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎባቸው ኢትዮ ኒፖን ከተባለው ኩባንያ የተገዙ ናቸው፡፡

Palm_Oil_Import.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገር ውስጥ የሚታየው የዘይት ምርት ዋጋ ንረትና አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በመንግሥት በተላለፈው ውሳኔ ከተገዛው ውስጥ  የ5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት ሥርጭት እያከናወነ ነው፡፡

ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የምግብ ዘይት አምራች ኩባንያ በኮርፖሬሽኑ በኩል ተገዝቶ የቀረበው ይህ ምርት ኮርፖሬሽኑ በአጠቃላይ ውል ከተፈራረመበት 21.5 ሚሊየን ሊትር የዘይት ምርት ከታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ጀምሮ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የምርት ሥርጭት 2,389,660 ሚሊየን ሊትር ዘይት በኮርፖሬሽኑ የምርት ማከፋፈያ ማዕከላት አማካኝነት በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ጋምቤላ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከተሞች ተሠራጭቷል፡፡

የዘይት ምርቱ መንግሥት ባወጣው የዋጋ ተመን መሠረት በሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበራትና በተፈቀደላቸው አቅራቢዎች አማካኝነት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በተላለፈው ኮታ መሰረት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ነው እየቀረበ ይገኛል፡፡ ቀሪው ዘይት በተከታታይ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የሚሰራጭ ይሆናል፡፡

በሌላም በኩል ኮርፖሬሽኑ የአገር ውስጥ ገበያን በማረጋጋት ተልዕኮው በዓሉን በማስመልከት ነጭ ጤፍ እና የዳቦ ዱቄት ለመንግሥት ሠራተኞች፣ እና ለልዩ ልዩ ተቋማት  በዝቅተኛ  ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡