የምርት ጥራት ቁጥጥርና ክምችት እንክብካቤ መመሪያ ላይ ከኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና ዘርፎች ለተውጣጡ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡


የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ዓላማ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የጥራት ቁጥጥር ስራን ስርዓት ባለዉና በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ደንበኛን ለማርካትና የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነት ለማረጋገጥ መሆኑን ስልጠናውን የሰጡት በኮርፖሬሽኑ የምርት ጥራት፣ ቁጥጥርና ክምችት እንክብካቤ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደመቀ ሰውነት አብራርተዋል፡፡


መመሪያው ሲዘጋጅ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ፣ መረጃ በመሰብሰብና ትንታኔ በመስራት ያሉትን መልካም ተሞክሮዎችን እንዲሁም ክፍተቶችን በመለየት ተያያዥነት ያላቸዉን የመንግስትና የህግ ድንጋጌዎ፣ ሀገር-አቀፍና አለም-አቀፍ ደረጃዎችንና ስምምነቶችን፣ መልካም ተሞክሮዎችን ወ.ዘ.ተ ታሳቢ መደረጉን አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡

 

 

 2.jpg

photo_2023-12-15_11-37-55.jpg

 

የኮርፖሬሽኑ ንብረት በአግባቡ እንዲታወቅ ለማስቻል የቋሚ ንብረት መለያ ኮድ አሰጣጥ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለማኔጅመንት ቀርቦ ጸድቋል፡፡ የጸደቀውን መመሪያ አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከዋናው መሥሪያ ቤትና ከሁሉም ዘርፎች ለተውጣጡ የንብረትና ፋይናንስ ሠራተኞች ተሰጠ፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናውን ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሠራ ተገኘወርቅ እንደገለጹት እንደ ኮርፖሬሽን የንብረት መለያ ኮድ መስጠት በማስፈለጉ መመሪያ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ ሥልጠናው የተዘጋጀው በመመሪያው ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቋሚ ንብረት መለያ ኮድ አሰጣጥ መመሪያው አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከዓላማዎቹ መካከል ንብረትን ከብክነት መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም ንብረትን በቀላሉ ለማስተዳደር ማስቻል የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የፌዴራል ፖሊስ አባላት በተገኙበት ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ጥቅምት 5/ 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡30 በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ-ስርዓት በማካሄድና የኢትዮጵያን ብሄራዊ የህዝብ መዝሙር በመዘመር አከበሩ፡፡

የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ እቴነሽ ገ/ሚካኤል ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክተው ባደረጉት አጭር ገለጻ አገራችን ኢትዮጵያ ከቅኝ ገዥ ወራሪዎች ድንበሯን ተከላክላ፤ ነፃነቷን አስከብራ የኖረች የጥቁር ሀገሮች መመኪያ መሆኗን አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ ሦስትን መነሻ በማድረግ የወጣው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 በየዓመቱ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንዲከበር መደንገጉንና በዚህም መሠረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ/ም በዓሉ በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ ቀን እንዲከበር መወሰኑን ጠቅሰዋል።

 

 

 

 

ተጨማሪ ምስሎችን እዚህ ይመልከቱ፡፡

Management_News2.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስራ አመራር የ2016 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ፡፡ በኮርፖሬሽኑ ስር የሚገኙ ዘርፎች፣ የዋና መ/ቤትና የኮርፖሬት ሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሩብ ዓመት እቅድ ክንውን በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመቱ በአጠቃላይ ሊገዛው ያቀደው መሠረታዊ የምርት አቅርቦት መጠን ብር 1,442,305,115 ዋጋ ያለው 297,648 ኩንታል ሲሆን በዚህ ወቅት ብር 2,778,723,940 ዋጋ ያለው 498,031 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 167 በመቶ፤ በዋጋ ደግሞ 193 በመቶ ማከናወኑ በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

ሽያጭን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ብር 2,920,244,100 ዋጋ ያለው 543,820 ኩንታል መሠረታዊ ምርትና አገልግሎት ለማሰራጨት አቅዶ ብር 2,665,653,200 ዋጋ ያለው 483,427 ኩንታል ምርትና አገልግሎት በማሰራጨት ዕቅዱን በመጠን 89 በመቶ በዋጋ ደግሞ 91 በመቶ አከናውኗል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማውን በመሩበት ወቅት በሩብ ዓመቱ በትንሽ ጥረት የታየው አፈጻጸም አበረታች እንደሆነ ገልጸው በቀሪዎቹ ዘጠኝ ወራት የበለጠ በመስራት የላቀ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ቀጣይ ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆን አለባቸው በማለት በዝርዝር ካቀረቧቸው ጉዳዮች መካከል ግዢና ሽያጭን ሁልግዜ በሁሉም መደብር/ቅርንጫፍ መተግበር፣ ገቢን ማሳደግ፣ እያንዳንዱን ፈጻሚ በውጤት መመዘን፣ ወጪ ቆጣቢ ስልት መጠቀም፣ ነባሩን በማጠናከር አዳዲስ የምርት አቅርቦት ላይ መስራት፣ የፋይናንስ ሥራን ማጠናቀቅ (IFRS/ኦዲት)፣ ትልቅ ገቢ የሚያመጡ ስራዎች ላይ ማተኮር የሚሉት ይገኙበታል፡፡

GridArt_20231012_110101692.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በተሟላ ሁኔታ ለመፈፀም ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ይገኛል፡፡ ከምርት ግዥና ሽያጭ ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ በነሐሴ ወር በሀገር ውስጥ እና በኤክስፖርት ገበያ ለመሸጥ ያቀደው የእህል፣ ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና አትክልት እና ፍራፍሬ ምርት መጠን 89 ሺህ ኩንታል በብር 556.4 ሚሊዮን ሲሆን 164.8 ሺህ ኩንታል በብር 925.1 ሚሊዮን በመሸጥ ዕቅዱን በመጠን 185 በመቶ እንዲሁም በዋጋ 166 በመቶ አከናውኗል፡፡

 

በአጠቃላይ በነሐሴ ወር በሀገር ውስጥ 45.2 ሺህ ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ሲሚንቶና የምግብ ዘይት በብር 217.8 ሚሊዮን ለመሸጥ ዕቅድ ተይዞ 123.9 ሺህ ኩንታል እህል፣ ቡና፤ ሲሚንቶና የምግብ ዘይት በብር 556.52 ሚሊዮን በመሸጥ በመጠን 276 በመቶ፤ በዋጋ 255 በመቶ ለማከናወን ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በወሩ ውስጥ 576 ኩንታል ቡና በብር 16,758,720 ኤክስፖርት በማድረግ ገቢ ተገኝቷል፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ በነሐሴ ወር ላይ ለመሸጥ ያቀደው የአትክልትና ፍራፍሬ እና የፍጆታ ምርቶች መጠን 26.8 ሺህ ኩንታል በብር 174.5 ሚሊዮን ሲሆን በዚህ ወቅት 16.4 ሺህ ኩንታል በብር 181.9 ሚሊዮን በመሸጥ የዕቅዱን በመጠን 61 በመቶ በዋጋ ደግሞ 104 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ በነሐሴ ወር ላይ ለመሸጥ ያቀደው የፍጆታ ሸቀጦች መጠን 17.13 ሺህ ኩንታል በብር 164.7 ሚሊዮን ሲሆን በዚህ ወቅት 22.8 ሺህ ኩንታል በብር 169.9 ሚሊዮን በመሸጥ ዕቅዱን በመጠን 133 በመቶ በዋጋ ደግሞ 103 በመቶ አከናውኗል፡፡