የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዕውቅናውን ያገኘው ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን ምዕተ ዓመት አከባበር በማስመልከት “ማኅበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ቃል በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከኅዳር 24 እስከ 26/2016 ዓ/ም ሲካሄድ በቆየው የ2016 የአሠሪና ሠራተኛ ጉባዔ መገባደጃ ላይ በተካሄደው የዕውቅና መርኃ ግብር ነው፡፡

ከ200 በላይ በግብርና፣ በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ ምቹ የሥራ ሁኔታ ለፈጠሩ የግልና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ አሠሪዎች እንዲሁም የሠራተኞች ፌዴሬሽኖች በተወዳደሩበት በዚህ የዕውቅና መርኃ ግብር ላይ ኮርፖሬሽኑ ብልጫ ካገኙ ተቋማት መካከል አንዱ በመሆን ዕውቅና አግኝቷል፡፡

ሽልማቱን የኮርፖሬሽኑ የሕግ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችና አሠራር ማሻሻያ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ከሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እጅ ተቀብለዋል፡፡ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ክብርት ሚንስትሯ ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠርና ሠላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዕውቅናውን በተመለከተ አቶ ይርጋሸዋ በሰጡት አስተያየት ኮርፖሬሽኑ ለሠራተኛው ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ እንደ ካይዘን ያሉ የለውጥ መሣሪያዎችን ጭምር በመጠቀም እየሠራ መሆኑን፤ አንዲሁም ከሠራተኛ ማኅበሩ ጋር ዘላቂ የሆነ መልካም ግንኙነትን እንዲኖር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሠራተኛውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሠፊ ሥራዎችን ማከናወኑን አስረድተዋል፡፡ የተገኘው ዕውቅናና ሽልማትም በቀጣይ በመስኩ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለማጠናከር የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ በካይዘን ትግበራና ውጤታማነት እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ዘርፍ አገግሎት አሰጣጥ ባበረከተው አስተዋጽዖ ተሸላሚ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ይርጋሸዋ፤ አሁንም የተገኘው የዕውቅናና ሽልማት ምቹ የሥራ አካባቢን ለሠራተኛው ከመፍጠር ባለፈ በሌሎች መስኮችም ውጤታማ አፈጻጸምን በማጎልበት ኮርፖሬሽኑ ምርትና አገልግሎቱን በተሻለ ጥራትና ተደራሽነት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ የሚያበረታታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

7a.jpg

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 7b.jpg

 

 

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው 14ኛው የአዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የእርሻና ምግብ ንግድ ትርኢት ከህዳር 27 -29 /2016 ዓ/ም በሚሊኒየም አዳራሽ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በንግድ ትርኢቱ ላይ በመሳተፍ ጥራታቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ የሚያቀርባቸውን ናሙና የእህልና ቡና ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች እና የፍጆታ ሸቀጦችን ለጎብኚዎች አስተዋውቋል፤ ከአምራች ድርጅቶች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮችም የንግድ ትርኢቱን በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

 

6a.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በህዳር ወር 2016 ዓ.ም 280,248 ኩንታል ምርት ለገበያ አቀረበ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በወሩ የምርት ግዥና ሽያጭ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የግዥ ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ሕዳር ወር 101,124 ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍጀታ ዕቃ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት በብር 515,030,325 ለመግዛት አቅዶ 48,150 ኩንታል ምርት በብር 299,343,563 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 48 በመቶ በዋጋ ደግሞ 58 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 477,599 ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የፍጆታ ዕቃዎች ለመግዛት አቅዶ የነበረ ሲሆን 593,917 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን 124 በመቶ ማከናወን ተችሏል፡፡

የአጠቃላይ ሽያጭ አፈጻጸምን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ሕዳር ወር በሀገር ውስጥ እና በኤክስፖርት ገበያ ለመሸጥ ያቀደው የእህል፣ ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና አትክልት እና ፍራፍሬ ምርት መጠን 125,234 ኩንታል በብር 718,853,059 ሲሆን 280,248 ኩንታል በብር 1,360,169,866 በመሸጥ ዕቅዱን በመጠን 224 በመቶ እንደዚሁም በዋጋ 189 በመቶ አከናውኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በወጭ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ለመሸጥ ያቀደው አጠቃላይ መጠን 555,837 ኩንታል ምርት ሲሆን የተሸጠው መጠን 946,502 ኩንታል ወይም የዕቅዱን 170 በመቶ ነው፡፡

GridArt_20231012_110101692.jpg

በኮርፖሬሽኑ የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ከዋና መ/ቤትና ከሁሉም ዘርፎች ለተውጣጡ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ታህሳስ 8/ 2016 ዓ/ም ተሰጠ፡፡


በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የህግ፣ ማህ/ጉ/አሰ/ማሻ/ም/ዋ/ሥ/አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ኮርፖሬሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስራው እየሰፋ በመምጣቱ አሰራሩ በመመሪያ እንዲታገዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ መመሪያዎች በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፣ በአፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮችን በየጊዜው መመዝገብ እና በየደረጃው ላለ አካል ማሳወቅ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ አክለውም ስልጠናው ወጥ የሆነ ግንዛቤ ይዞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል ዓላማ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የግዢ መመሪያው ሲዘጋጅ ነባሩ የግዢ መመሪያ፣ የመንግስት የግዢ መመሪያዎች እንዲሁም የሌሎች ተቋማት የግዢ መመሪያዎቸ በግብአትነት መወሰዳቸው ተመልክቷል፡፡ የግዢ አፈጻጸም መመሪያው ዘጠኝ ምእራፎች ያሉት ሲሆን ከያዛቸው ዓላማዎች መካከል አንድ ወጥ የሆነ የግዢ አፈጻጸም ስርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬሽኑን የአሰራር ሂደት ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ ነው፡፡

5.jpg

ተኪ የሰው ሀብት አፈፃፀም መመሪያ (Succession Planning Manual) ላይ ከኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና ከሁሉም ዘርፎች ለተውጣጡ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡


በኮርፖሬሽኑ ወሳኝ በሆኑ የሥራ መደቦች ክፍተት ሳይፈጠር በአጭር ጊዜ ተቋማዊ አሰራርን ተገንዝቦ ሊሰራ የሚችል አመራርና ሰራተኛ በማፍራት ዘላቂ ዕድገት፣ የተሻለ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ፈፃሚዎች ወደፊት የሚመጡበትና ትክክለኛ ሰው በትክክለኛ ቦታ የሚገኝበት የሰው ሐይል ሙሌት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ተኪ የሰው ሀብት አፈፃፀም መመሪያ ተዘጋጅቶ በሥራ አመራር ቦርድ መጽደቁ በሥልጠናው ተመልክቷል፡፡


በየደረጃው የሚቀመጡ የሥራ ኃላፊዎች እና ቁልፍ ሠራተኞች በየጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች ሥራቸውን በሚለቁበት ወቅት የሥራ መደቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መሙላት አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቁልፍና ወሳኝ በሆኑ የሥራ መደቦች ላይ ክፍት የሥራ መደብ ተፈጥሮ ሳይሸፈን ሲቀር ደግሞ የኮርፖሬሽኑን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ሊገታ ይችላል፡፡ በመሆኑም ክፍተትንና የአሠራር ጉድለት ለመፍታት የሚረዳ አጠቃላይ መመሪያ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ተኪ የሰው ሃብት አፈጻጸም መመሪያ መዘጋጀቱን የኮርፖሬት አሰራር ዘዴና የአገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ትእዛዙ ኃ/ጊዮርጊስ ገልጸዋል፡፡


በቀጣይም ለሚመለከታቸው የኮርፖሬሽኑ የቡድን መሪዎችና የክልል ቅርንጫፍ አመራሮች መመሪያውን አስመለክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

1.jpg