የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ጅግጅጋ የገበያ ማዕከል በደረሰው ቃጠሎ ለተጎዱ ወገኞች ማቋቋሚያ የሚሆን የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ/ም አደረገ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ህ/ማህ/ጉ/አሰ/ማሻ/ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ለኢንጂነር ዚያድ አብዲ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባና የዕርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ይህንን ድጋፍ ያበረከተው የህዝብ አለኝታነቱንና ወገናዊነቱን ለማሳየት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

12.jpg

11a.jpg11b.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞች በ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና በ2016 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡ በውይይት መድረኩ የዋና መ/ቤት፣ የአራቱም ዘርፎችና የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ የክልል ግብይት ማእከላትና ጣቢያዎች አመራርና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የውይይት መድረኮቹ በድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ መቀሌ፣ አዳማ እና አዲስ አበባ ከተሞች በጥቅምት እና ህዳር 2016 ዓ.ም ተካሂደዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከህዳር 10-11/ 2016 ዓ.ም በተካሄደው የውይይት መድረክ መክፈቻ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በ2015 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑን የሚያሻግሩ እቅዶች ተነድፈው ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው ከቀደሙ ዓመታት የላቀ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ የተገኘው ስኬት የጠቅላላ አመራርና ሰራተኞች ውጤት መሆኑን ጠቁመው ይህም ለሌላ ውጤት የሚያነሳሳ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ክንውን ሪፖርት፣ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች፣ የተወሰዱ መፍትሔ እርምጃዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከሰራተኞች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ዋና ሥራ አሥፈጻሚው በመድረኩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልእክት በ2016 በጀት ዓመት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ግዥን ሳያቋርጡ ማከናወን፣ ሽያጭን በስፋት ማካሄድ፣ ፈጣን አገልግሎት መስጠት፣ የተለያየ የገበያ ትስስር መፍጠር የሚሉት በዋናነት ይገኙበታል፡፡

ከኮርፖሬሽኑ ምስረታ ጀምሮ በእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ፍርዱ አየለ እና በግዥና ማማከር አገልግሎት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚነት ያገለገሉት አቶ ክፍሌ ተስፋዬ ከኮርፖሬሽኑ በጡረታ ምክንያት በመልቀቃቸው የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ኅዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም በግሎባል ሆቴል ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡


በሽንት ፕሮግራሙ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በጡረታ ምክንያት ኮርፖሬሽኑን የለቀቁትን የቀድሞ ስራ አስፈጻሚዎች ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ቀሪ ጊዜያቸውን ከቤተሰባቸው ጋር በደስታ እንዲሳልፉ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡


አቶ ፍርዱ አየለ ባስተላለፉት መልእክት በኮርፖሬሽኑ ውስጥ በነበራቸው ኃላፊነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተሰጣቸው እውቅና የነሱ ብቻ ሳይሆን አሁን ላለው የስራ አመራር አባል ሁሉ መሆኑን ጠቁመው የተደረገው ሽኝት ለካ ልፋቴ ዋጋ አለው እንድል አድርጎኛል ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡


አቶ ክፍሌ ተስፋዬ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ እውቀት ያገኙበት ቦታ እንደሆነ ጠቅሰው በአካል ቢርቁም በመንፈስ ግን ሁሌም ከኮርፖሬሽኑ ጋር እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

9b.jpg9a.jpg

በአዲስ አበባ ከተማ ህዳር 11/ 2016 ዓ.ም በተካሄደው የኮርፖሬሽኑ የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ክንውንና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ ማጠቃለያ ላይ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ አብዲ ሙመድ በተገኙበት በቦርዱ ውስጥ የተጓደለን የሰራተኛ ተወካይ ለመተካት ምርጫ ተካሄደ፡፡

ምርጫውን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ከዚህ ቀደም የሰራተኛ ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አማረ ዳምጤ እና አቶ ሳለጌታ በላይ መልቀቂያ በማስገባታቸው እንደሆነ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ገልጸዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም ከዚህ ቀደም በቦርዱ ውስጥ ሁለት የሰራተኛ ተወካዮች የነበሩ ሲሆን የሚወከለው ሰራተኛ አንድ እንዲሆን በመወሰኑ ምክንያት ከዚህ ቀደም ተወካይ የነበሩት ሁለት ግለሰቦች ለሰራተኛው ክብር ሲሉ ጠቅላላ ጉባኤው የሚወክለውን ሰራተኛ እስኪመረጥ ራሳቸውን ከቦርድ አባልነት ማግለላቸውን አብራርተዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱን የመሩት አቶ አብዲ ሙመድ በሰራተኛው የሚወክለው ግለሰብ የሰራተኛውን ጥቅም የሚያስከብር፣ የተቋሙን ተልእኮ የሚያሳካ፣ ተቋሙ የበለጠ እንዲያድግና ትርፋማ ሆኖ እንዲቀጥል የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ አርአያ የሚሆንና ብቃት ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸው የሚወከለው ሰራተኛ በሚፈለግበት ጊዜ በቀላሉ እንዲገኝ ከአዲስ አበባ እንዲሆን አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የእጩዎች ምርጫና የድምጽ መስጠት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

የዕጩዎችን ብዛት በተመለከተ በተሰጠ ድምጽ 3፣ 5 እና 6 የሚሉ አማራጮች ቀርበው 5 የሚለው በአብላጫ ድምጽ የተወሰነ ሲሆን ከቀረቡት እጩዎች መካከል ወ/ሮ ኤልሳቤት ታደሰ በ274 አብላጫ ድምጽ ተመርጠዋል፡፡ አቶ አበዋ ጌትነት በ142 ድምጽ በተጠባባቂነት ተመርጠዋል፡፡

10.jpg

በአብላጫ ድምጽ የተመረጡት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ታደሰ

GridArt_20231012_110101692.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በ 2016 በጀት ዓመት የጥቅምት ወር ካከናወናቸው የምርት ግብይት እና ሽያጭ አፈጻጸም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

የግዢ አፈጻጸም

ኮርፖሬሽኑ ጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም 95.66 ሺህ ኩንታል የእህል፣ የቡና፣ የፍጀታ ዕቃ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በብር 481.02 ሚሊዮን ለመግዛት አቅዶ 49.32 ሺህ ኩንታል በብር 388.96 ሚሊዮን በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 52 በመቶ በዋጋ ደግሞ 81 በመቶ አከናውኗል፡፡ በወሩ ከተደረገው ግብይት የምግብ ዘይት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ስኳር እንዲሁም የተለያዩ የእህል ዓይነቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ያለፉት አራት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 393.57 ሺህ ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የፍጆታ ዕቃዎች ለመግዛት አቅዶ 546.33 ሺህ ኩንታል ምርት በመግዛት ዕቅዱን 139 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡

የሽያጭ አፈጻጸም

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት በጥቅምት ወር በሀገር ውስጥ እና በወጪ ንግድ ለመሸጥ ያቀደው የእህል፣ ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና አትክልትና ፍራፍሬ ምርት መጠን 117.44 ሺህ ኩንታል በብር 668.93 ሚሊዮን ሲሆን 185.78 ሺህ ኩንታል በብር 990.20 ሚሊዮን በመሸጥ ዕቅዱን በመጠን 158 በመቶ እንዲሁም በዋጋ 144 በመቶ አከናውኗል፡፡ በወሩ ከተከናወነው የምርት ሽያጭ የምግብ ዘይት፣ የፍጆታ እቃዎች፣ እህልና ሲሚንቶ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ያለፉት አራት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በወጪ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ለመሸጥ ያቀደው አጠቃላይ መጠን 505.11 ሺህ ኩንታል ሲሆን 666.25 ሺህ ኩንታል ወይም የዕቅዱን 131 በመቶ አከናውኗል፡፡